Sunday, October 15, 2017

በሱማሌ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ በደረሰ የሽብር ጥቃት 85 ሰዎች ሞቱ፡፡

በሱማሌ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ በደረሰ የሽብር ጥቃት 85 ሰዎች ሞቱ፡፡

 ባህር ዳር፡ ጥቅምት 5/2010 ዓ/ም (አብመድ)ሞቃዲሾ ላይ በደረሰው አደጋ ሀላፊነቱን የወሰደ ባይኖርም ሀገሪቱ በተደጋጋሚ የአልቃኢዳ እና አልሸባብ ኢላማ ሆና ቆይታለች፡፡ በተፈጸመው የሽብር ጥቃት ሞቃዲሾ ሀዘን ላይ ነች፡፡ሶማሊያ በፕሬዝዳንት ሙሀመድ ፋርማጆ አማካኝነት 3 የሀዘን ቀናትን አውጃለች፡፡ የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ተነግሯል፡፡ ምንጭ፡-ቢቢሲ

ደብረ ማርቆስ ከተማ ከኦሮምያ እንቦጭን ለማስወገድ ለመጡት ወጣቶች ውብ አቀባበል አድርጋለች፡፡

ደብረ ማርቆስ ከተማ ከኦሮምያ እንቦጭን ለማስወገድ ለመጡት ወጣቶች ውብ አቀባበል አድርጋለች፡፡

 ዛሬ ቀኑ ጥቅምት 2/2010 ዓ/ም ነው፡፡ጥቅምት 2 ደግሞ ኢትዮጵያውን አርበኞች ወራሪውን የጣልያን ፋሺስት በመጣበት እንዲመለስ ‹‹ወረኢሉ ከተህ ላግኝህ›› በተባለው መሠረት የጉዞ መነሻቸው ዕለት ነው፡፡ ዛሬም በጣና ህልውና ላይ የመጣውን ወራሪ ቅጠል ለማስወገድ ከኦሮምያ ክልል ከተለያዩ አካባቢዎች የተሰባሰቡ ወጣቶች ወደ አማራ ክልል በመጓዝ ላይ ናቸው፡፡በአንድነት በመተሳሰብና በመፈቃቀር የተጀመረው ጉዞ ጣና ላይ …ጣናን ባለበት ለማጽናት የሁሉንም ይሁንታ በሚፈልገው ጣና ተገኝተው የድርሻቸውን ይወጣሉ፡፡ወጣቶቹ በአማራ ክልል በሚደርሱበት ቦታ ሁሉ አቀባበል ውብ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡፡፡ የአባይ ገባር የሆነው ጣና ጉዳቱ ከጨመረ መጨረሻው በህዳሴው ግድብ ላይ ሌላ የአደጋ ስጋት ይሆናል፡፡ጣናን መታደግ አባይን መታደግ ነው፡፡ ሁሌም ለስራ ዝግጁ የሆነው የወጣት ጉልበት በእምቦጭ አረም ላይ ዘምቶ ውጤት እንደሚያስመዘግብ ጥርጥር የለውም ፡፡

Saturday, September 9, 2017

የቡርማ ሙስሊሞች ጉዳይ


ከጊዜህ ላይ 90 ሴኮንድ ወስደህ ስለ ቡርማ ሙስሊሞችን ችግር ብታውቅ ምን ይመስልሃል?
ታሪኩ ባጭሩ ይህን ይመስላል!
3,000,000 ሙስሊሞች የሚኖሩባት አራካን የተሰኘች አንዲት ሃገር ነበረች። ከዚች ሃገር ጎረቤት በሆነችው ቡርማ የአራካን ሙስሊሞች በሚያደርጉት ዳዕዋ ምክንያት እስልምና አየተስፋፋ ሄደ። ቡርማ ውስጥ አብዛሃኛው ማህበረሰብ የቡድሃ እምነት ተከታይ ነው። በ1784 /ማለትም ከዛሬ 230 አመታት በፊት/የቡርማ ቡድሂስቶች በአራካን ሙስሊሞች ላይ ባሳደሩት ቂም ምክንያት ወረራ በመፈፀም ብዙ ሙስሊሞችን ገደሉ። አራካንንም ወደ ቡርማ በማስገባት መጠሪያዋን ሚንማር የሚል ስም አደረጉ። ሙስሊሞች አነስተኛውን ቁጥር የሚይዙ ሲሆን ብዛታቸው ከ 3 ― 4 ሚሊዮን ይደርሳል።


በአንፃሩ ደግሞ ቡድሂስቶች 50,000,000 ይሆናሉ።
ሙስሊሞች የራሳቸውን መንደር በማበጀት የንግድ ልውውጦች እና የራሳቸውን ማህበራዊ ህይወት መምራት ጀመሩ። በዚቹ መንደር ውስጥ የተለያዩ ማህበራት ያሉ ሲሆን መሳጂዶችንና ዱኣቶችን ይደጉማሉ።

አሁንም የቡርማ ቡድሂስቶች ወደ ሙስሊሞች መንደር በመዝመት ከሃገር ለማስወጣት እንቅስቃሴ ጀመሩ። ብዙም ሳይቆይ አሰቃቂ የሆነ ግድያ (እርድ) ፈፀሙ። ይህም የሆነው በሙስሊሞች አካባቢ በመዘዋወር ሰዎችን የሚያስተምሩ ፣ ኒካህ የሚያስሩ ፣ ቁርኣን የሚያስቀሩ ወደ አስር የሚጠጉ ሃፊዞችንና ዳኢዎችን በመያዝ ብርቱ የሆነ ድብደባ ፈፀሙባቸው።

ይህም አልበቃ ብሏቸው ሰውነታቸውን በሳንጃ ተጫወቱበት። እንደውም ያንደኛውን ምላስ በገመድ ካሰሩ በኋላ ያለምንም ርህራሄ ጎለጎሉት። ከዚያም ሁሉንም ተራ በተራ እግር እና እጃቸውን በመቆራረጥ ገደሏቸው። ይሄን ሁሉ ግፍ የሚፈፅሙት ለ ኢስላምና ሙስሊሞች ካላቸው ጥብቅ ጥላቻ የተነሳ ነው።

ሙስሊሞችም ከኢማሞቻቸው፣ ከኸጢቦቻቸው እና ከዱኣቶቻቸው ለመከላከል እንቅስቃሴ አደረጉ። ቡድሂስቶችም በአፀፋው የሙስሊሞችን መንደር በእሳት አያያዙት። በእሳት አደጋው የተቃጠሉ ቤቶች ቁጥር ወደ 2600 ገደማ ደርሷል። በዚህም ቃጠሎ ምክንያት የሞተው ሞቶ የሸሸውም ሸሸ። ወደ 90,000 የሚደርሱ ሙስሊሞች በየብስም በባህርም ወደ ሌሎች አገሮች ተሰደዱ።

መታረዱም ይሁን መገደሉ አሁንም ድረስ እንደቀጠለ ነው። ሚስቶቻቸው፣ እህቶቻቸው፣ ልጆቻቸው… አይናቸው እያየ የአስገድዶ መደፈር ወንጀል ተፈፅሞባቸዋል።

Wednesday, September 6, 2017

የ10ኛ ክፍል የፈተና ውጤት ማያ

| የ10ኛ ክፍል የፈተና ውጤት ዛሬ ይለቀቃል

Grade 10 Student Information only.

Use Your Registration No. to check your result.


Click here for Grade 12 result.




ከላይ ካልሰራልወት  ከዚሀ ይጫኑ  እናመሰግናለን!!





© 2017 - NEAEA-Ministry Of Education.
Developers

Monday, September 4, 2017

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ






ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ በራያ የቢራ ማስታወቂያ ላይ በትወና መልክ መሳተፌ የሚታወቅ ነው ሆኖም ለተፈጠረው ስህተት ብዙሁን ቅሬታቸውን በኔ ላይ እያሰሙ ነው:: ነገር ግን እኔ በዚህ ማስታወቂያ ላይ በትወና መልክ ከመቅረብ ውጪ ተፈጠሩ የተባሉ ስህተቶች ላይ አለመሳተፌን ለመግለፅ እወዳለው :: አጥፍቼም ከሆነ ይቅርታ ጠይቃለው ::

Source: ሰላም ተስፋየ facebook account

Wednesday, August 2, 2017

​ቅዱስ ጊዮርጊስ ታደለ መንገሻን ሲያስፈርም አሜ መሐመድን ለማስፈረም ተስማምቷል

የፕሪምየር ሊጉ ቻምፒዮን ቅዱስ ጊዮርጊስ ደደቢትን ለመቀላቀል ተስማምቶ የነበረው ታደለ መንገሻን ባልተጠበቀ ሁኔታ ሲያስፈርም አሜ መሐመድን ለማስፈረም ተስማምቷል፡፡













ያለፉትን ሁለት የውድድር አመታት በአርባምንጭ ያሳለፈው ታደለ መንገሻ ወደ ቀድሞ ክለቡ ደደቢት ለመመለስ ተስማምቶ የነበረ ቢሆንም ባልታወቀ ምክንያት ሳይፈርም ቀርቶ በ2000 እና 2001 የውድድር አመታት ወደተጫወተበት ቅዱስ ጊዮርጊስ ተመልሶ የ2 አመታት ኮንትራት መፈራረሙን የቅዱስ ጊዮርጊስ ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ አስታውቋል፡፡

ሌላው ለቅዱስ ጊዮርጊስ ፊርማውን ያኖራል ተብሎ የሚጠበቀው አሜ መሐመድ ነው፡፡ አሜ ከጅማ አባ ቡና ጋር የ1 አመት ውል የነበረው በመሆኑ ተጫዋቹ ለጅማ አባ ቡና የውል ማፍረሻ 1,000,000 ብር ለመክፈል ተስማምቶ መልቀቂያ ተቀብሏል፡፡ በቀጣዮቹ ጊዜያትም በይፋ ለክለቡ የሚፈርም ይሆናል፡፡

መቐለ ከተማ ሁለት አዳዲስ ተጫዋቾች አስፈረመ

አዲሱ የፕሪምየር ሊግ ክለብ መቐለ ከተማ ጫላ ድሪባ እና ታደለ ባይሳን የግሉ አድርጓል፡፡












ጫላ ድሪባ አዳማ ከተማን ለቆ የተጠናቀቀውን የውድድር አመት በወልድያ ያሳለፈ ሲሆን ከበድሩ ኑርሁሴን ጋር በመፈራረቅ በወልዲያ አጥቂ መስመር ላይ ከአንዷለም ንጉሴ ጋር ሲሰለፍ ቆይቶ ኮንትራቱን በማጠናቀቁ ወደ መቐለ ተጉዟል ፡፡

ሌላው ለክለቡ የፈረመው ታደለ ባይሳ ነው፡፡ ከፋሲል ከተማ ጋር ወደ ፕሪምየር ሊጉ አብሮ ያደገው የመሀል ተከላካዩ ታደለ ዘንድሮ የሊጉ ክስተት በነበረው ፋሲል ከተማ በስፍራው ከከድር ኸይረዲን ጋር በመፈራረቅ የተጫወተ ሲሆን በተሰለፈባቸው ጨዋታዎች ቡድኑን በአምበልነት ሲመራ እንደነበር ይታወሳል፡፡
መቐለ ከተማ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ማደጉን ካረጋገጠ ወዲህ በተጫዋቾች ዝውውር ላይ ተሳትፎን እያደረገ የሚገኝ ሲሆን የሁለቱን ተጫዋቾች ጨምሮ እስካሁን ያስፈረማቸው ተጫዋቾች ቁጥር 5 ደርሷል፡:

ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ 6 ተጫዋቾችን አስፈረመ

ለመጀመርያ ጊዜ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ያደገው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በዛሬው እለት የ5 አዳዲስ ተጫዋቾችን ፊርማ ሲያጠናቅቅ አንድ ተጫዋች በቋሚነት አስፈርሟል፡፡ እንየው ካሳሁንንም ለማስፈረም ተቃርቧል፡፡


ያለፉትን ሁለት አመታት በኢትዮ ኤሌክትሪክ ያሳለፈው ዋለልኝ ገብሬ ወደ ወልዋሎ ማምራቱ የተረጋገጠ ተጫዋች ነው፡፡ የመሀል አማካዩ በኤሌክትሪክ የአማካይ ክፍል ላይ ከበኃይሉ ተሻገር ጋር በመፈራረቅ አመዛኞቹ ጨዋታዎች ላይ መሰለፍ ችሏል፡፡

ቢንያም አየለ ሌላው የክለቡ ፈራሚ ነው፡፡ አዳማ ከተማ በ2007 ወደ ፕሪምየር ሊግ በተመለሰበት አመት 3ኛ ሆኖ እንዲያጠናቅቅ ከተጠባባቂ ወንበር እየተነሳ ባስቆጠራቸው ወሳኝ ጎሎች የረዳ ቢሆንም ቀጥሎ ባሉት አመታት ግን ጥቂት ጨዋታዎች ላይ ብቻ ተሰልፎ ተጫውቷል፡፡

ተስፋዬ ዲባባ ወደ ወልዋሎ ያመራ ሌላው ተጫዋች ነው፡፡ የቀድሞው የሙገር ሲሚንቶ ፣ ኢትዮጵያ ቡና እና ንግድ ባንክ የመሀል ተከላካይ በድሬዳዋ ከተማ ያለፉትን ሁለት አመታት ያሳለፈ ሲሆን በቋሚነትም ቡድኑን አገልግሏል፡፡



ክለቡ ከፕሪምየር ሊጉ በተጨማሪ ሁለት ተጫዋቾችን ከከፍተኛ ሊጉ አስፈርሟል፡፡ ግብ ጠባቂው ዘውዱ መስፍን የባህርዳር ከተማ ውሉን አጠናቆ ወደ ወልዋሎ አምርቷል፡፡ ከዚል ቀደም በቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ መተሀራ ስኳር እና ኢትዮጵያ ክለቦች በፕሪምየር ሊጉ የተጫወተው ዘውዱ ወደ ሊጉ ዳግም ተመልሷል፡፡ እዮብ ወልደማርያምም የወልዋሎ ንብረት የሆነ ተጫዋች ነው፡፡ እዮብ ወልዲያ ወደ ፕሪምየር ሊጉ እንዲገባ ቁልፉን ሚና ከተጫወተ በኋላ ክለቡን ለቆ አመቱን በአማራ ውሀ ስራ አሳልፏል፡፡

ወልዋሎ ካስፈረማቸው አዳዲስ ተጫዋቾች በተጨማሪ አሳሪ አልመሀዲን በቋሚነት አስፈርሟል፡፡ አሳሪ በውድድር አመቱ አጋማሽ ከድሬዳዋ ከተማ በውሰት አምርቶ መልካም ግልጋሎት ማበርከቱን ተከትሎ በቋሚነት ክለቡን ተቀላቅሏል፡፡

እንየው ካሳሁን ለክለቡ ለመፈረም ከስምምነት የደረሰ ተጫዋች ነው፡፡ የቀኝ መስመር ተከላካዩ በአዲስ አበባ ከተማ ያለውን የአንድ አመት ውል ማፍረስ የሚጠበቅበት ሲሆን ውሉን በስምምነት አፍርሶ መልቀቂያውን ሲቀበል ለወልዋሎ በይፋ ይፈርማል ተብሏል፡፡

ወልዋሎ ከቀናት በፊተ የግ መስመር ተከላካዩ ሮቤል ግርማን በሁለት አመት ኮንትራት ማስፈረሙ የሚታወስ ሲሆን የበረከት አማረ ፣ ሳምሶን ተካ እና ኤፍሬም ጌታቸውን ውል ማደሱ ታውቀል፡፡

Monday, July 31, 2017

አባባ ተስፋዬ በ94 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ::

አባባ ተስፋዬ በ94 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ::













ጤና ይስጥልኝ ልጆች!
የዛሬ አበባዎች፤ የነገ ፍሬዎች!
እንደምን አላችሁ ልጆች!
አያችሁ ልጆች!
የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የልጆች ክፍለ ጊዜ ዝግጅት እናንተን ለማስደሰት ልክ በሰዓቱ ይገኛል።
አባባ ደሞ የልጆች ሰዓት እንዳያልፍባቸው በሩጫ ዲ ዲ ዲ ከተፍ ፤ እናንተ ደግሞ ቆማችኃል። ይሄ በጣም ጥሩ ነው ልጆች። አንድ አባት ሲመጣ በአክብሮት መነሳት አስፈላጊ ነው ።
ደህና ሁኑ ልጆች!
ደህና ሁኑ ልጆች!
ነፍሳቸውን በገነት ያኑርልን!

Tuesday, May 23, 2017

ተፈጥሯዊ የእርግዝና መቆጣጠሪያ

ተፈጥሯዊ የእርግዝና መቆጣጠሪያ

የወር አበባ ኡደትን ማዕከል ያደረገ
ውድ የሳይቴክ ፔጅ ተከታታዮች፡፡ የወር አበባ ኡደትን ማዕከል ያደረገ የወሊድ መቆጣጠሪያ ይሄንን ይመስላል፡፡
• የወር አበባ መፍሰስ ከጀመረበት ቀን አንስቶ እስከ አምስተኛው ቀን ድረስ መደበኛ የወር አበባ ጊዜ ነው፡፡ ይሄንን ጊዜ ጨምሮ የወር አበባው ከጀመረበት ቀን እስከ 8ኛው ቀን ድረስ (የመጀመሪያዎቹ ሰባት ቀናት) በአንፃራዊነት እርግዝና አይፈጠርም፡፡ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት በዚህ ወቅት ያለመፈጠር እድሉ ከ95-100% እንደሆነ ይደርሳል፡፡
• ከ8ኛው ቀን እስከ 11ኛው ቀን ባሉት ሶስት ተከታታይ ቀናት ደግሞ በአንፃራዊነት እርግዝና ሊፈጠር ይችላል፡፡ ጥናቶቹ የሚጠቁሙትም እርግዝና የመፈጠሩ እድል ከ40-60% ይደርሳል፡፡
• ከ11ኛው ቀን ጀምሮ እስከ 17ኛው ቀን ድረስ ባሉት ተከታታይ 6 ቀናት እርግዝና የመፈጠር እድሉ እጅግ በጣም ከፍተኛ ነው፤ ከ80% በላይ፡፡
• ከ17ኛው ቀን አንስቶ እስከ 20ኛው ቀን ድረስ ባሉት 3 ተከታታይ ቀናት ደግሞ በአንፃራዊነት እርግዝና ሊፈጠር ይችላል፡፡ ጥናቶቹ የሚጠቁሙትም እርግዝና የመፈጠሩ እድሉ ከ40-60% እንደሆነ ነው፡፡
• ከ20ኛው ቀን አንስቶ የወር አበባ እስከሚመጣበት ጊዜ ድረስ እርግዝና አይፈጠርም፡፡ በዚህ ወቅት እርግዝና ያለመፈተሩ እድል ከ95-100% ይደርሳል፡፡
• የሴቷ እንቁላል በወር አበባው ኡደት እኩሌታ ቀን ላይ (28 ከሆነ 14ኛው ቀን ላይ) ዝግጁ የሚሆን ሲሆን ከ12-24 ሰዓታት ለሚሆን ጊዜ ለፅንስ ዝግጁ እንደሆነ ሊጠብቅ ይችላል፡፡ በአንፃሩ የወንዱ የዘር ፍሬ ከወሲብ በኋላ በሴቷ ማህፀን ውስጥ ከ3 እስከ 5 ቀናት ሊቆይ የሚችል ሲሆን በአንድ ላይ ሲደመር ከአምስት ቀን እስከ ሰባት ቀናት ለሚሆን ጊዜ የእርግዝናው እድልን እጅግ ከፍተኛ ይሆናል ማለት ነው፡፡
ሌሎችም ያንብቡት። በተን በተን አርጉት።

Saturday, May 20, 2017

ለራስ ምታት ፍቱን የሆኑ 9 የምግብ አይነቶች

ለራስ ምታት ፍቱን የሆኑ 9 የምግብ አይነቶች


















1. ሃብሃብ

ሃብሃብ - በውስጡ እጅግ ብዙ ፈሳሽ እና ማዕድናትን የያዘ ከፍራፍሬዎችም በትልቅነቱ የሚታወቅ ነው፡፡ በተለይ ከአዲስ አበባ ወደ ናዝሬትና ሐዋሳ መስመር ሲሄዱ በመንገድ ዳር ተሸክመው ሲሸጡት እንመለከታለን፡፡ ሞክረውት እንደሆነ ባላውቅም በጉዞው ወቅት ለሚኖረው ሙቀት እና የውሃ ጥም ሁነኛ መፍትሄ ሆኖ ይገኛል፡፡ ከዚህ ጥቅሙም ባሻገር ለራስ ምታት ፍቱን መድሃኒት መሆኑ በባለሙያዎች ተጠንቶ ተቀምጧል፡፡ የሪደርስ ዳይጀስት መጽሔት በቅርቡ ባሰፈረው ጽሑፍ ሃብሃብ ለራስምታት ፍቱን ያስባለው ከፍተኛ የውሃ እና ማዕድናት በተለይም ከፍተኛ የማግኒዚየም ማዕድን መጠኑ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ለራስምታት ከሚያጋልጡ ምክንያቶች አንዱ ድርቀት ወይም በሰውነት ውስጥ በቂ ፈሳሽ ያለመኖሩ ነው፡፡ ይህ ፍራፍሬ ደግሞ ይህን ችግር በደንብ ይፈታል፡፡ ከራስ ምታት ክኒን ይልቅ በቅርብ ሃብሃብ ከተገኘ በደቂቃዎች ውስጥ ከራስምታቱ እረፍትን ይሰጣል ብለው ባለሞያዎቹ ይናገራሉ፡፡

2. ዝንጅብል

ዝንጅብል ላይ የሚደረጉ ምርምሮች ገና በቅርቡ የተጀመሩ ቢሆንም በውስጡ የደም ቧንቧዎችን መቆጣት እና ህመም የሚቀንሱ መድሃኒቶች ውስጥ ካሉ ኬሚካሎች ጋር ተመሳሳይ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን ተመራማሪዎች ማግኘት ችለዋል፡፡ በተለይ በከባድ የራስ ምታት ወቅት የደም ቧንቧዎችን መቆጣት በማስከተል ራስምታቱ እንዲቀሰቀስ የማድረግ ተግባር ያላቸውን ፕሮስታግላንዲን የሚሰኙ ንጥረ ቅመሞች መጠን በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነስ ራስ መታቱን እንደሚያስታግስ የሪደርስ ዳይጀስት መጽሔት ይገልጣል፡፡ ራስ ምታቱን ሙሉ በሙሉ ባያቆመው እንኳ ከራስ ምታት ጋር የሚመጡ ደስ የማይሉ እንደ ማቅለሽለሽ አይነት ስሜቶችን በቶሎ ይቀንሳል፡፡ ለዚህ ሳይሆን አይቀርም ኢትዮጵያውያን ያለጥናቶቹ ውጤትም ቀድመው ለሆድ ህመም እና ማቅለሽለሽ ዝንጅብል አኝክበት ሲሉ የኖሩት!

3. ቡና

ለአንዳንዶች ቡና ፍቱን የራስ ምታት መድሃኒት ሲሆን ማይግሬይን ላለባቸው አንዳንድ ሰዎች ላይ በብዛት ሲወሰድ ማይግሬይኑን የሚቀሰቅስበት አጋጣሚ አለ፡፡ ሳይንሱ ሁሉንም የቡና ምስጢር ፈትቶ ባይጨርስም እስካሁን ባሉት ጥናቶች መሰረት ግን ቡናን ፍቱን የራስ ምታት መድሃኒት አድርጎ መውሰድ ይቻላል፡፡ መጠኑን በልክ ማድረግ አብሮ ሊታሰብበት ይገባል፡፡ ለከባዱ የራስ ምታት ማይግሬይን የሚታዘዙ ክኒኖች ውስጥ የቡና ዋና ንጥረ ነገር ካፌይን ይገኛል፡፡ ስለሆነም ቡና ለራስ ምታት በመፍትሄነት መቅረቡ አስደናቂ ነገር አይሆንም፡፡ ይሁንና መጠኑ በበዛ ቁጥር ራስ ምታትን ከማስታገስ ይልቅ ጭራሽ ሊቀሰቅሰው ይችላል፡፡ እጅግም ወፍራም ያልሆነ አንድ ወይም ሁለት ስኒ ቡና ከሁለት ክኒን የተሻለ ተፈጥሯዊ መድሃኒት ሆኖ ተገኝቷል፡፡

4. ስፒናች

ትኩስ ስፒናች ጎመን ቅጠል በውስጡ የያዛቸው ቅመሞች ራስ ምታትን በማስታገስ ብቻ ሳይሆን የደም ግፊት መጠንን በመቀነስም በቀደመው ጊዜ ጥቅም እንደነበራቸው መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ አትክልትና ፍራፍሬ በርካሽ ለሚገኝባቸው እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ሀገራት ይህ ጥሩ ዜና ይመስላል፡፡ በውጪው ዓለም ስፒናችን አብስሎ ወይም በትኩሱ ከቲማቲም ጋር ከትፎ በመብላት ብቻ ሳይሆን ጨምቆ ከመጠጣትም ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ የቅርብ ጊዜ ጥናቶች ደግሞ ይህ ፍቱን አትክልት ለራስ ምታትም ፈጣን መፍትሄ ይሰጣል ብለዋል፡፡ ቢፈልጉ ጨምቀው ከሻይ ጋር አለዚም ባዶውን ወይም ትኩሱን ቅጠል ሰላጣ እንደሚያዘጋጁት አዘጋጅተው ቢመገቡት ከራስ መታቱ ፋታ እንዲያገኙ እንደሚረዳዎት የተደረጉ የመጀመሪያ ደረጃ ጥናቶች አመልክተዋል፡፡

በተጨማሪም
5. ሙዝ፣

6. እርጎ፣

7. ጉበት፣

8. ድንች እና

9. ቃሪያም ራስ ምታትን በመቀነስ በኩል ፍቱን እንደሆኑ በጥናት ተረጋግጥዋል፡፡

ሌሎችም ያንብቡት። በተን በተን አርጉት።
ጤና ለሁሉም!

Tuesday, May 16, 2017

የቪዛ መስፈርቶች ለኢትዮጵያ ዜጎች

የቪዛ መስፈርቶች ለኢትዮጵያ ዜጎች በየአገሩ ይለያያሉ። የኢትዮጵያ ዜጎች ወደ ብዙዎቹ አገራት ለመግባት፣ አስቀድሞ ከዚያው አገር ኤምባሲ ወይም ቆንስላ በፓስፖርት ውስጥ የቪዛ (መግቢያ ፈቃድ) ማሕተም ማግኘት አስፈላጊነት ነው። ሆኖም አንዳንድ አገር ያለ ምንም ቪዛ ሂደት ኢትዮጵያውያን ለተወሰነ ጊዜ እንዲጎብኙ ይፈቅዳል፣ እንዲሁም አንዳንድ አገር ኢትዮጵያውያን እዚያ በደረሱበት ጊዜ የመግቢያ ፈቃድ ይሰጣል።



ማስታወሻ - መስፈርቶቹ እንደ መንግሥታት በቶሎ ሊቀየሩ ይቻላል።


ያለ ቪሳ መግባት የፈቀዱ አገራት

  • ኬንያ - ለ3 ወር ያለ ቪሳ መጎብኘት ለኢትዮጵያውያን ይፈቀዳል
  • ሃይቲ - ለ3 ወር " " " "
  • ሴኔጋል - ለ3 ወር " " " "
  • ቤኒን - ለ90 ቀን " " " "
  • ሴይንት ቪንሰንትና ግሬናዲንስ - ለ30 ቀን " " " "
  • ሲንጋፖር - ለ30 ቀን " " " "
  • ማይክሮኔዥያ - ለ30 ቀን " " " "
  • ፊሊፒንስ - ለ30 ቀን " " " "
  • ዶመኒካ - ለ21 ቀን " " " "

ኢትዮጵያውያን በደረሱበት ጊዜ የጉብኝት ቪሳ የሚሰጡ አገራት

እነዚህን አገራት ከመግባት በፊት ቪሳ ማግኘት አስፈላጊ አይደለም። ሌሎች አገራት ሁሉ ግን ከመግባት አስቀድሞ ቪሳ ማግኘት አስፈላጊነት ነው።
  • ኮሞሮስ
  • ካቦ ቨርዴ
  • ጂቡቲ
  • ኡጋንዳ
  • ሞሪታኒያ
  • ርዋንዳ
  • ደቡብ ሱዳን
  • ማዳጋስካር (የ90 ቀን ጉብኝት ቪሳ)
  • ቦሊቪያ (የ90 ቀን " ")
  • ጊኔ-ቢሳው (የ90 ቀን " ")
  • ኒካራጓ (የ90 ቀን " ")
  • ሞሪሸስ (የ60 ቀን " ")
  • ታጂኪስታን (የ45 ቀን " ")
  • ሰይንት ሉሻ 6 ሳምንት " "
  • ሞዛምቢክ (የ30 ቀን " ")
  • ጋና (የ30 ቀን " ")
  • ካምቦዲያ
  • ላዎስ (የ30 ቀን " ")
  • ምሥራቅ ቲሞር (የ30 ቀን " ")
  • ታይላንድ (የ15 ቀን " ")
  • ኢራን (የ15 ቀን " ")
  • ቶጎ (የ7 ቀን " ")
  • ሳሞአ - ለ60 ቀን " " " "
  • ሲሸልስ - ለ3 ወር " " " "
  • ቱቫሉ - ለ1 ወር " " " "
  • ማልዲቭስ - ለ30 ቀን " " " "
  • ፓላው - ለ30 ቀን " " " "

በኢንተርኔት ላይ ቪዛ የሚስጡ አገራት

  • ጂዮርጂያ
  • አንቲጋ እና ባርቡዳ
  • አውስትራሊያ
  • ጋቦን
  • ስሪ ላንካ

የኢትዮጵያ ዜጎች የማይፈቅዱ አገራት

  • ኩዌት

Monday, May 15, 2017

የጌሾ መድሃኒታዊ ጥቅም እና ሌሎች ጥቅሞች



ጌሾ በአፍሪካ ብቻ የሚበቅል በተለይ በኢትዮጵያና በደቡብ አፍሪካ የሚገኝ ተክል ነው። በኢትዮጵያ ጠላና ለጠጅ ሲጠመቅ ጌሻ ይገባል። የሚበቅለውም ከባህር ወለል በላይ 1400-3200 ሜትር ላይ ነው።

መድሃኒታዊ ጥቅም

-ቆረቆርና ሌሎች የፈንገስ በሽታወችን በደቀቀ ፍሬውና ቅጠሉ በመቀባት ለማዳን ይቻላል - ህጻናት እንጥላቸው ከተቆረጠ በኋላ ህመማቸውን ለማስታገስ አፋቸው ውስጥ የጌሾ ቅጠል ይደረጋል -ቂጥኝ በሽታን ለመከላከል -ሆድ ድርቀት ለማስወገድ - ሥሩ ደምን ለማጥራት ያገለግላል

ሌሎች ጥቅሞች

የጌሾ ግንድ በጣም ጠንካራ ስለሆነ ለተለያዩ የእንጨት ውጤቶች ሊያገለግል ይችላል። የጌሾ ዛፍ በምንጮች አካባቢ ቢተከል የመሬት መሸርሸርን ሊከላከል ይችላል። ከእርሻ ማሳ ዳርቻ ላይ በመትከልም የመሬትን ንጥር ነገር ከነፋስ እና ከዝናብ መከላከል ይቻላል። የጌሾ አበቦች በንቦች ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነት ስላላቸው የጌሾ ተክል ለንብ እርባታና ለማር ምርት ከፍተኛ ግልጋሎት ሊሰጥ ይችላል።

የሩዝ ቅቅል አዘገጃጀት ለ3 ሰው


አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች 3 የቡና ስኒ (300 ግራም) ሩዝ 1 መካከለኛ ጭልፋ (150 ግራም) የደቀቀ ቀይ ሽንኩርት 6 የሾርባ ማንኪያ ዘይት 1 የሻይ ማንኪያ ጨው 1 የሻይ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ፡፡




 አዘገጃጀት 
1. ሩዙን በደንብ አጥቦ ደረቅ እስኪል ማንጠፍጠፍ፤ 
2. ዘይት በደረቅ ብረት ድስት ውስጥ አሙቆ ቀይ ሸንኩርቱን በመጨመር ማቁላላት፤ 
3. ሩዙን በላዩ ጨምሮ ደርቆ ቀላ ያለ መልክ እስኪያወጣ ማቁላላት፤ 
4. ሩዙ በተለካበት ዕቃ እጥፍ የሚሆን ውሃ መጨመር፤ 
5. አንዴ ብቻ አማስሎ እስኪበስል መተው፤ 
6. ጨውና ቁንዶ በርበሬውን ጨምሮ ማስተካከል፤ 
7. ውሃው መጦ ሲበስል ማውጣት፤ 
8. ውሃው መጦ ሩዙ ካልበሰለ በማንኪያ መሃሉ ላይ ወጋ አድርጎ የፈላ ውሃ በመጨመር እንደገና እስኪመጥ መጠበቅና ለገበታ ሲፈለግ ከሶሱ ጋር ደባልቆ ወይም ለየብቻ ማቅረብ፡፡

Sunday, May 14, 2017

15 የሎሚ ህክምናዊ ገጸበረከቶች

ሎሚ በቫይታሚን ሲ እና ቢ፣ፎስፈረስ፣ኘሮቲንና ካርቦሀይድሬት የበለፀገ የፍራፍሬ ነው።ሎሚ ፍላቮይድ የተባለ ንጥረ በውስጡ ይዟል ይህ ንጥረ ነገር የካንሰር በሽታን ይከላከላል። ሎሚን በብዙ መልኩ ልንጠቀምበት እንችላለን።ከነዚህም መካከል የሎሚ ሻይ፣የሎሚ ኬክ፣ የሎሚ ዘይትና የሎሚ ሳሙና ይጠቀሳሉ።ከነዚህም በተጨማሪ የህክምና ጥቅሙም ላቅ ያለ ነው።
ህክምናዊ ጥቅሞቹ እንደሚከተሉት ናቸው፦

1. የጉሮሮ ኢንፌክሽንን ለመከላከል
ሎሚ የጉሮሮን ኢንፌክሽን ከሚከላከሉልን ፍራፍሬዎች አንድ ሲሆን የፀረ ባክቴሪያ (ባክቴሪያን የመከላከል) ሀይል አለው እናም የሎሚ ጭማቂ ከውሀ ጋር ቀላቅለው ወይም በሻይ መልክ ቢወዱት ጥቅሙ ላቅ ያለ ነው።
2. ምግብን ለማንሸራሸርና የሆድ ድርቀትን ለመከላከል ይረዳናል
ወዲያው የተዘጋጀ የሎሚ ጭማቂ የምግብ አለመፈጨትንና የሆድ ድርቀትን ይከላከላል። በምግብዎ ውስጥ ትንሽ ጠብታ ሎሚ መጨመር ተገቢ ነው ነገር ግን ሎሚ ከወተት ጋር መቀላቀል እንደሌለብዎት እንዳይዘነጉ።ሎሚ ደምን
ያጣራል በተጨማሪም ጥሩ ማፅጃ( ማጠቢያ) በመሆን ያገለግላል።
3. ትኩሳትን ለማስታገስ
ወዲያው የተዘጋጀ የሎሚ ጭማቂ በብርድ፣በሳልና በትኩሳት ለሚሰቃዩ ሰዎች ፍቱን መድሀኒት ነው።የሰውነታችንን ትኩሳት ቶሎ ቶሎ እንዲያልበን በማድረግ ያስታግሳል። እኩል መጠን ያላቸውን የተፈጥሮ ማርና የሎሚ ጭማቂ በመቀላቀል ወይም የሎሚ ሻይ በመጠቀም ሳልን መቀነስ የሚቻል ሲሆን
ከባድ የጉሮሮ በሽታን ለማስታገስ ይረዳናል።
4. ለጥርስ እንክብካቤ ይጠቅመናል
የሎሚ ጭማቂ ለጥርስ እንክብካቤና ህክምና ያገለግላል። የጥርስ ህመምበሚያጋጥምበት ጊዜ ትኩስ(fresh) የሎሚጭማቂ በህመሙ ቦታ ላይማድረግ ፍቱን ማስታገሻነው።በተፈጥሮ የሎሚ ጭማቂ ድድን ማሸት ከድድ መድማት ችግርና ከመጥፎ የአፍ ጠረን ይታደግዎታል በተጨማሪም
ሁልጊዜ ጥርስዎን ቢቦርሹበት ተጠቃሚ ይሆናሉ።
5. የቆዳ እብጠትን ያስታግሳል
የሎሚ ጭማቂ የቆዳ እብጠትን የሚከላከል ሲሆን ሰውነታችን ላይ ባለው እባጭ ላይ ያድርጉት በተጨማሪም ከዉሀ ጋር የተቀላቀለ የሎሚ ጭማቂ
መጠጣት ለኩላሊት ጠጠር እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው።
6. የተቃጠለ ቁስልን ያስታግሳል
ወዲያው የተዘጋጀ የሎሚ ጭማቂ በተቃጠለው የሰውነታችን ቁስል ላይ ማድረግ ጠባሳ (scar) እንዳይዝ (እንዳይኖር) ያደርጋል። ሎሚ ሰውነታችንን
የማቀዝቀዝ ባህሪ ስላለው በቃጠሎ ምክንያት የሚመጣን የመለብለብ (የማቃጠል) ስሜት ያስታግሳል።
7. ውስጣዊ የደም መድማትን ይከላከላል
የሎሚ ጭማቂ ውስጣዊ መድማትን ይከላከላል ምክንያቱም ሎሚ ፀረ ጀርምና ፀረ ባክቴሪያ ባህሪ ስላሉት ነው። የአፍንጫ መድማትን ለመከላከል
በሎሚ ጭማቂ የተነከረ ጥጥ በአፍንጫ ቀዳዳ ውስጥ ከተው ለትንሽ ደቂቃዎች ማቆየት ይመከራል።
8. የወባና አተት(Cholera) በሽታዎችን ለመከላከል
ሎሚ ደምን የማጣራት አቅም ስላለው እንደ ወባና አተት ያሉ በሽታዎችን ይከላከላል።
9. እግር ዘና/ፈታ እንዲል ያደርጋል
ሎሚ ጠንካራ ሽታና ፀረ ባክቴሪያ ኬሚካላዊ ባህሪ አለው ስለዚህ ለብ ባለ ውሀ ውስጥ የሎሚ ጭማቂ አድርገው እግርዎን መንከር እግርዎ ዘና እንዲል
ያደርገዋል።
10. ለቆዳ እንክብካቤ
የሎሚ ጭማቂ እርጂናን የሚከላከል ሲሆን የቆዳ መሸብሸብና ቆዳ ላይ ያሉ ትንንሽ ጥቁር ነጠብጣቦችን እንዲሁም የተለያዩ ችግሮችን የፀረ ጀርምና ፀረ ባክቴሪያ ባህሪ ስላለው እንዲወገድ በማድረግ ይሳተፋል። የፀሀይ ጨረርን ለመከላከል ወዲያው የተዘጋጀ የሎሚ ጭማቂ ፊትን መቀባት ጠቃሚ ነው።ወዲያው የተዘጋጀ የሎሚ ጭማቂ ከማርና ውሀ ጋር በመቀላቀል መጠጣት።
11. ለመገጣጠሚያና ጡንቻ ህመሞች
ይህ ህመም ብዙ ጊዜ በእድሜ ገፋ ያሉ ሰዎች ላይ የሚስተዋል ሲሆን ሎሚ የማይፈለጉ የሰውነት ፈሳሾችን እንዲወገድ በማድረግ የመገጣጠሚያና ጡንቻ ህመሞችን ያስታግሳል ከዚህም በተጨማሪ በሰውነታችን ውስጥ ያሉትን ባክቴሪያና መርዛማ ነገሮች እንዲወገድ ያደርጋል።
12. ክብደትን ይቀንሳል
የሎሚ ጭማቂን ለብ ካለ ውሀና ማር ጋር በመቀላቀል መጠጣት የሰውነት ክብደትን ለመቀነስ ይረዳናል። የሎሚ ጭማቂ የሰውነት ክብደትን ለመቀነስ ይረዳናል ብላችሁ ብትጠይቁኝ አዎ በትክክል ይቀንሳል እልዎታለሁ።
13. የአተነፋፈስ ችግርን ያስተካክላል
ሎሚ የአተነፋፈስ ችግርን ያስተካክላል። ሎሚ በቫይታሚን ሲ የበለፀገ ስለሆነ የአስምና የመተንፈሻ አካላት ችግር ላለባቸው ሰዎች በጣም ጠቃሚ ነው።
14. የደም ግፊት ይቀንሳል
ወዲያው የተዘጋጀ የሎሚ ጭማቂ መጠጣት በውስጡ ፓታሲየም ስላለው በልብ ህመም ለሚሰቃዩ ሰዎች ጠቃሚ ነው። ከፍተኛ ደም ግፊትን፣
መንገዳገድ(ማዞር)ና ማቅለሽለሽን በመቆጣጠር አእምሮና ሰውነታችን ዘና እንዲል ያደርጋል።
15. ለፀጉር እንክብካቤ
የሎሚ ጭማቂ ፀጉርን በማከም ከፍተኛ ድርሻ አለው እንደ ፎረፎር፣ የፀጉር መነቃቀልና ከራስ ቅል ጋር የተያያዙ ችግሮችን ለመከላከል የሎሚ ጭማቂን
የራስ ቆዳ አናት ላይ መቀባት ጠቃሚ ነው። የሎሚ ጭማቂ ፀጉርን መቀባት ፀጉራችን አንጸባራቂ እንዲሆን ያደርገዋል።
መልካም ጤንነት!!
ለበለጠ የጤና መረጃ የፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ።

የመቀሌ ከነማ እና የባህርዳር ከነማ እግር ኳስ ቡድኖች በመቀሌ ከተማ የተካሄደው ጨዋታ እረብሻ በመነሳቱ ምክንያት ተቋረጠ





ትላንት ቅዳሜ ግንቦት 2 - 2009 ዓ.ም በመቀሌ ከነማ እና የባህርዳር ከነማ እግር ኳስ ቡድኖች በመቀሌ ከተማ የተካሄደ ሲሆን ጨዋታው መሃል ላይ እንደተቋረጠ የዜና ምንጮች አስታወቁ::እንደ ዜና ምንጮቹ ገለጻ ከሆነ በመቀሌ በተደረገው  ጨዋታን ምክንያቱ በውል ባይታወቅም የሁለቱም ክለቦች ደጋፊዎች እና ተጨዋቾች ተጋጭተዋል ::በተፈጠረ ግጭትም ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቁ ተጨዋቾችና ደጋፊዎች ተጎድተዋል ። 





 






 





ዝርዝር ምክንያቱን እንደደረሰን የምናቀርብ መሆኑን እናሳዉቃለን