ደብረ ማርቆስ ከተማ ከኦሮምያ እንቦጭን ለማስወገድ ለመጡት ወጣቶች ውብ አቀባበል አድርጋለች፡፡
ዛሬ ቀኑ ጥቅምት 2/2010 ዓ/ም ነው፡፡ጥቅምት 2 ደግሞ ኢትዮጵያውን አርበኞች ወራሪውን የጣልያን ፋሺስት በመጣበት እንዲመለስ ‹‹ወረኢሉ ከተህ ላግኝህ›› በተባለው መሠረት የጉዞ መነሻቸው ዕለት ነው፡፡
ዛሬም በጣና ህልውና ላይ የመጣውን ወራሪ ቅጠል ለማስወገድ ከኦሮምያ ክልል ከተለያዩ አካባቢዎች የተሰባሰቡ ወጣቶች ወደ አማራ ክልል በመጓዝ ላይ ናቸው፡፡በአንድነት በመተሳሰብና በመፈቃቀር የተጀመረው ጉዞ ጣና ላይ …ጣናን ባለበት ለማጽናት የሁሉንም ይሁንታ በሚፈልገው ጣና ተገኝተው የድርሻቸውን ይወጣሉ፡፡ወጣቶቹ በአማራ ክልል በሚደርሱበት ቦታ ሁሉ አቀባበል ውብ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡፡፡
የአባይ ገባር የሆነው ጣና ጉዳቱ ከጨመረ መጨረሻው በህዳሴው ግድብ ላይ ሌላ የአደጋ ስጋት ይሆናል፡፡ጣናን መታደግ አባይን መታደግ ነው፡፡
ሁሌም ለስራ ዝግጁ የሆነው የወጣት ጉልበት በእምቦጭ አረም ላይ ዘምቶ ውጤት እንደሚያስመዘግብ ጥርጥር የለውም ፡፡
No comments:
Post a Comment