Thursday, January 11, 2018

የታላቁን ንጉሥ ልደት ለመዘከር የወርሃ ጥርን መግቢያ ለመይሳው ካሳ፤ ቋረኛው አንበሳ-የጀግንነት ልኩ፤

የታላቁን ንጉሥ ልደት ለመዘከር የወርሃ ጥርን መግቢያ ለመይሳው ካሳ፤ ቋረኛው አንበሳ-የጀግንነት ልኩ፤
ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም የጥር ወርን መጀመሪያ ለታላቁ ንጉሥ ለንጉሠ ነገሥት ዐፄ ቴዎድሮስ እንስጠው ብሎ ጀግናውን መተረክ ጀምሯል፡፡ ቋረኛው አንበሳ የጀግንነት ልኩ ሲል የተወለደባትን ስፍራ የማስታወሻው መጀመሪያ አድርጓታል፡፡ | ሄኖክ ስዩም በድሬ ቲዩብ
አንዷን ኢትዮጵያ ሰላሳ አርባና ሀምሳ ቦታ ቦጫጭቀው ለዕለት ደስታቸው የሚኖሩ መሳፍንት በበዙበት ዘመን አንድ ሰው ተወለደ፡፡
የዚህን ጀግና እትብት የቀረበረች ቋራ እንደምን የታደለች ናት፡፡ ቋራ ከዚያም ቀድሞ የጀግኖች ከዚያም በኋላ የጀግኖች ምድር ናት፡፡
የጥር ወርን በራፍ ታላቁን ምድር እያነሳን እንዘክረዋለን፡፡
ቋራና እንደክብሩ ከስሙ አስቀድሞ ለመጠራት የመጀመሪያው ሰው መይሳው አልነበረም፤ ለምሳሌ በጎንደር ዘመን የነበሩት የእቴጌ ምንትዋብ ልጅ ቋረኛው ኢያሱ በሚል ይጠሩ ነበር፡፡
ራሳቸው እኒያ ብርሃን ሞገሳ የተባሉት ብርቱ ሴት የጎንደር ዘመን የፖለቲካ እቴጌም ቋረኛ ናቸው፡፡ በሱሲኒዮስና በሰርጸ ድንግል ዜና መዕዋሎች የቋራን ወንድ የጦር ሜዳ ውሎ ማየት ይቻላል፡፡
ቋራ በርሃ ነው፤ ግን ደግሞ ደን የተጠቀጠቀበት፤ የዓይማ ወንዝ በረከት ያረሰረሰው፤ አባታቸው ሐይሉ ወልደጊዮርጊስ የቋራ ተወላጅ እና ስም ያላቸው ጀግና ነበሩ፡፡ እናታቸው ደግሞ የእንፍራንዟ አትጠገብ ናቸው፡፡ አትጠገብ የደንቢያ ባላባት ልጅ ናቸው፡፡
መይሳው በልጅነታቸው ፊደል የቆጠሩት ሥርዓት የተማሩት ማህበረ ስላሴ ገዳም ነው፡፡ ለዚህ ነው አረብኛ ቋንቋ እንጂ ሃይማኖት እንዳልሆነ የገባቸው፡፡
ማህበረ ሥላሴ በቋራ ምድር የሚገኝ በአብርሐ ወ አጽበሐ የተተከለ የታላላቅ ቅዱሳን አድራሻ ነው፡፡ ገዳሙ ድንበር ላይ ነው የሚገኘው፤ ድንበር ጥሶ ስለሚገባ ጠላት መይሳው ፊደል በሚማሩበት የልጅነት እድሜ የሀገር ዳር ድንበር ጉዳይንም አብረው እያጠኑ አደጉ፡፡
ዛሬ ገደባችሁ ብላ ጠዋት ማታ የምትዝተው ግብጽ የመይሳው ካሳ የልጅነት ቃታ መለማመጃ የጀግንነት ልኩን መስፈሪያ ነበረች፡፡
በወጣትነቱ የተሳተፈባቸው ውጊያዎች ግብጽ በሱዳን የኢትዮጵያን ድንበር ስትዘልቅ ሱዳን ድረስ ገብቶ አደብ ያስገዛት የነበረው ታሪክ ሺ ቦታ ተቆራርጣ የየመሳፍንቱ የአንገት ጌጥ በሆነችው ኢትዮጵያ ከዳር ዳር ናኘ፤ ይህንን ለመሰለ ጀግና ልጅን ቀድሞ መዳር የቀደመችዋ ኢትዮጵያ መሪዎች የፖለቲካ ዘዴ ነውና፤ እቴጌ መነን የልጅ ልጃቸውን ለወጣቱ ጀግና ለመዳር ልጃቸውን ራስ አሊን አሳመኑ፤ ቋራ የበጌምድር አማች ሆነ፡፡
የደሃ ደካማ የለውም የተባለው መይሳውም እንደተባለው በረታ፤ ምንትዋብን ካገባ በኋላ በዋለበት የጦር ሜዳ ሁሉ ድል ለእሱ ሆነች፡፡
ከእግዜር በታች የተባሉ መሳፍንት እያንዳንዱ ቀን እግሩ ስር የሚወድቁበት ክፍ ቀን ሆነ፡፡ ብዙ ቦታ ለብዙ እኔ ባይ መሳፍንት የሆነችዋ ሀገር ዳግም መልካም ቀን መጣላት፡፡
በጌ ምድር ከራስ ጉግሳ አንደርታ ከራስ ወልደ ጊዮርጊስ ጎን ቆም የአንድ ሀገር ልጅ ሁለት ጎራ የሚዋደቅበትን የታሪክ ቁስል የሚጠግን የብርሃን ጭላንጭል ታየ፡፡
ከጉራምባ እስከ መከሁ ለፍልሚያ የወጣው መይሳው ማታ ድሉን ማጣጣም ጀመረ፡፡
ይህ ጀግና ለኢትዮጵያ የተሰጣት ጥር ስድስት ቀን 1811 ዓ.ም. ነበር፡፡ ከአማቾቹ አንድ ሙከት የተነሳው ጀግና ኢትዮጵያን ታህል ታላቅ ሀገር እጁ ገባች፤ ጥርን ለመታሰቢያነቱ ሰጥተንዋልና ቀጥለናል፡፡

ይህን ያውቁ ኖሯል❓❓❓ አርባ አራቱ ታቦት የሚለው ታሪክ መነሻው ምንድን ነው ?

በተለምዶ ‹‹ አርባ አራቱ ታቦት›› እያልን የምንጠራቸው አብያተ ክርስቲያናት ያሉት በጐንደር ከተማ ሲሆን ስማቸውም የሚከተለው ነው፡፡
1. ፊት ሚካኤል2. ፊት አቦ
3. አደባባይ ኢየሱስ
4. ግምጃ ቤት ማርያም
5. እልፍኝ ጊዮርጊስ
6. መድኃኔዓለም7. ቅዱስ ገብርኤል
8. ጠዳ እግዚአብሔር አብ
9. አባ እንጦንዮስ10. ደብረ ብርሃን ሥላሴ
11. አደባባይ ተክለሃይማኖት
12. ሠለስቱ ምእት
13. ልደታ ለማርያም
14. አጣጣሚ ሚካኤል
15. አቡነ ኤውስጣቴዎስ
16. ቅዱስ ሩፋኤል
17. ደፈጫ ኪዳነ ምሕረት
18. ቁስቋም ደብረ ፀሐይ
19. መጥምቁ ዮሐንስ
20. በኣታ ለማርያም
21. ቅዱስ ቂርቆስ
22. ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ
23. አባ ጃሌ ተ/ሃይማኖት
24. ፈንጠር ልደታ
25. ደብረ ምጥማቅ ማርያም
26. አባ ዐቢየ እግዚእ
27. ቅዱስ ፋሲለደስ
28. ሐዋርያት
29. ቀሃ ኢየሱስ
30. አርባዕቱ እንስሳት
31. ጎንደሮች ጊዮርጊስ
32. ጎንደሮች ማርያም
33. አበራ ጊዮርጊስ
34. ብላጅግ ቅዱስ ሚካሌል
35. አባ ሳሙኤል
36. አይራ ሚካኤል
37. ጓራ ዮሐንስ
38. ወረንግቦ ጊዮርጊስ
39. አሮጌ ልደታ
40. አዘዞ ተ/ሃይማኖት
41. ምንዝሮ ተ/ሀይማኖት
42. ሰራራ ማርያም
43. ዳሞት ጊዮርጊስ
44. ጫጭቁና ማርያም

አርባ አራቱ ታቦት የሚለው ታሪክ መነሻው ምንድን ነው ?
እውን ታቦት አርባ አራት ብቻ ?
ጎንደር በኢትዮጵያ የመንግሥት ታሪክ ከአክሱምና ላሊበላ ቀጥሎ ትልቋ የመንግሥት ማዕከል ነበረች፡፡ በመንግሥት ማዕከልነት የተቆረቆረችው በአፄ ፋሲል (1624-1660 ዓ.ም) ነው፡፡ ጎንደር የመንግሥት ማዕከል ብቻ ሳትሆን በጊዜው የመንፈሳዊ ትምህርት ማዕከልም ነበረች፡፡ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የመጻሕፍት እና የአቋቋም ትምህርት ይበልጥ የተስፋፋውና በየሀገሩ ያሉ ሊቃውንት በመናገሻ ከተማዋ ጎንደር በነገሥታቱ አማካይነት በመሰባሰባቸው ሲሆን ከዚያን ዘመን ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ መንፈሳዊ ትምህርት በስፋት የሚሰጥባት የትምህርት ማዕከል ለመሆን ችላለች፡፡
በአሁኑ ሰዓት በሰሜን ጎንደር በሚገኙ 21 ወረዳዎች ከ2117 ያላነሱ ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናት ሲኖሩ በዋና ከተማዋ ደግሞ ከ92 ያላነሱ አብያተ ክርስቲያናት ይገኛሉ፡፡ በአብነት ት/ቤት ረገድም የመጻሕፍት ጉባዔያት፣ የአቋቋም ምስክር፣ የቅኔ አብያተ ጉባዔያት እንዲሁም የዜማ ት/ቤቶች በከተማዋ እና በዙሪያዋ በሚገኙ ወረዳዎች ይገኛሉ፡፡ በአሁኑ ሰዓት በከተማዋ ከ92 ያላነሱ አብያተ ክርስቲያናት ቢኖሩም በአብዛኛው ስማቸው ደጋግሞ የሚነሳው የ44ቱ ብቻ ነው፡፡ በተለያየ ጊዜ በተለይም ጎንደርን ከማያውቁት ሰዎች ጋር ባደረኩት ውይይት 44ቱን ታቦታተ ጎንደርን በተመለከተ የተለያየ ግንዛቤ እንዳለ ለመገንዘብ ችያለሁ፡፡ አንዳንዶቹ በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙት የአብያተ ክርስቲያናት ታቦታት ስያሜ ብዛት ሲመስላቸው ሌሎቹ ደግሞ በጎንደር በጥምቀት በዓል ወደጥምቀተ ባህር የሚወርዱትን ብቻ ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ ጎንደር ከተማ እየኖሩም የ44ቱን ዝርዝር በውል የማያውቁ ብዙ ሰዎች ገጥመውኛል፡፡ አርባ አራቱ ታቦታተ ጎንደር ከቤተ መንግሥቶቹ በተጨማሪ ታሪካዊዋ ጎንደር የምትታወቅበት ቅርስ ነው፡፡ ጎንደር ከተማ በአፄ ፋሲል የመንግሥት ከተማ ከመሆኗ አስቀድሞ የአካባቢው ነዋሪዎች ተክለዋቸው የነበሩ አብያተ ክርስቲያናት ነበሩ፡፡ ለምሳሌ ቀሐ ኢየሱስ፣ አርባዕቱ እንስሳ፣ አበራ ጊዮርጊስ፡፡
ጎንደር የመንግሥት ከተማ ከሆነችበት እስከ ጎንደር ዘመን ማክተሚያ ፈፃሜ መንግሥት አፄ ተክለ ጊዮርጊስ (1772-1777) ድረስ 18 ነገሥታት የነገሱ ሲሆን እነዚህም አብዛኛዎቹ አብያተ ክርስቲያናትን አሠርተዋል፡፡ እንግዲህ 44 የሚባሉት አብያተ ክርስቲያናት ጎንደር የመንግሥት ከተማ ከመሆኗ አስቀድሞ የተተከሉበትን ጨምሮ እስከ ፈፃሜ መንግሥት ተክለ ጊዮርጊስ (1772-1777) ድረስ የተተከሉትን ብቻ ሲሆን ቁጥራቸውም 44 ነው፡፡ ከዚያ ወዲህ ከዘመነ መሣፍንት እስከ አሁን የተተከሉ በርካታ አብያተ ክርስቲያናት ቢኖሩም ከ44ቱ የሚቆጠሩ አይደሉም፡፡ በአጠቃላይ አርባአራቱ ታቦታተ ጎንደር በጎንደር ዘመን በጎንደር ከተማና አካባቢው የሚገኙና የነበሩ 44 አብያተ ክርስቲያናት ጥቅል ስም ነው፡፡ ስለዚህ አርባ አራቱ ታቦት ሲባል ይህን ታሪክ ተከትሎ የመጣ ስያሜ እንጂ በቤተክርስትያናችን ቁጥር ስፍር የሌላቸው ታቦታት ነው ያሉት! ምክንያቱም ሁልጊዜም አዲስ ቤተ ክርስቲያን በሚሰራበት ጊዜ ታቦት ከእጽ ወይም ከእብነ በረድ ተቀርጾ በላዩ " ኢየሱስ ክርስቶስ አልፋ ኦሜጋ " ተብሎ ይጻፍበታል! የመጀመሪያውና የመጨረሻው ማለት ነው ፡፡ ይህ ቃል ከተጻፈበት በኋላ በኤፒስ ቆጶሱ እጅ ተባርኮና ሜሮን ተቀብቶ በመንበሩ ይሰየማል (ይቀመጣል) ፣በቅዳሴም ጊዜ ሕብስቱና ወይኑ ወደ ቤተ መቅደስ ሲገባ ቄሱ ሥርዓተ ቅዳሴውን የሚያከናውነው ሕብስቱን ሥጋ መለኮት ፣ ወይኑን ደመ መለኮት ወደ መሆን የሚለውጠው በዚህ በታቦቱ ላይ ነው ፡፡ሥጋዬን ብሉ ደሜንም ጠጡ እያለ ያመኑትን ሁሉ የሚጠራበት የምሕረት ምሥዋዕ (መሠዊ) ነው ፡፡ ታቦት በሐዲስ ኪዳን እውነተኛው የሕይወት ምግብ የክርስቶስ ሥጋና ደም የሚቀርብበትና የሚፈተትበት መሠዊያ ነው ፡፡
ስለዚህ በአርባ አራት ቁጥር ብቻ የሚወሰን ሳይሆን እልፍ አዕላፍ መሆኑን ልብ ልንል ይገባል! "ለሚጠይቃቹ ጥያቄ ሁሉ እንዴት መልስ መመለስ እንዳለባቹ ታውቁ ዘንድ ንግግራቹ ሁል ግዜ በጨው እንደተቀመመ በፀጋ ይሁን" ቆላስይስ 4:6።

የቋራው ካሳ-አንድ ሀገር የመፍጠር ህልምና የሀገር ልማት ረሃብ…

የቋራው ካሳ-አንድ ሀገር የመፍጠር ህልምና የሀገር ልማት ረሃብ፤ | ታላቁን ንጉሠ ነገሥት ዐፄ ቴዎድሮስን በጥር ወር የመጀመሪያ ሣምንት ለመዘከር ስለ ታላቁ ንጉሥ ትረካውን ቀጥሏል፡፡ አንድ ሀገር የመፍጠር ህልም በሀገር ልማት ርሃብ ላይ ሲል የታላቁን ንጉሥ ገድል ይተርክልናል፡፡ | ሄኖክ ስዩም |
ሁለት ነገር በአንዴ አርግዞ በየቁራጭ ርስቱ እፎይ ካለው መሣፍንት የቀደመ ህልም አለመ፡፡ አንድም ብዙ ሀገር አንድ ስለማድረግ፤ የምን ብዙ ሀገር ብሎ ከታሪክ የሚቃረን ብዙ ሰው ይኖራል፡፡
እውነቱን ግን አንደብቀውም፤ የጠገበ መስፍን ሁሉ ሰፈሩን ሀገር እያለ አንዷን ታላቅ ሀገር ሺ ቦታ በትነዋት የዋሁን ገበሬ ለየቀዬው ጦር ይሰለፍ ዘንድ አበሳውን አሳዩት፡፡ ደግሞም አንድ ሀገር የመመስረቱ ጉዞ የገዛ ቤተሰብ ከንቱ ምኞት ከማፍረስ ጀመረ፡፡
ከአራት መከራክር እስከ በጌምድር፣ ከጃናሞራ እስከ የጁ የነበረው የየራስ ህልም አንድ ህልም ሆነ፡፡ ወዲህ ደግሞ ሌላ ምኞት አለ፡፡ ዘምና የለማች ሀገር መፍጠር፤ ቱርክ በመሳሪያው የማያስፈራራት፤ ግብጥ በጥበቡ እንቅልፍ የማይነሳት፤ አውሮጳ በመላው የማያንበረክካት ሀገር መፍጠር፡፡ መይሳው የወንዜ ሰው አልነበረም፡፡ ስለ ወንዙ ሳይሆን ስለ ሀገሩ የሚጨነቅ መሪ ሆነ፡፡
የተበደሉት ከበቡት፤ የበደሉት ተዋጉት፡፡ ድል ለጭቁኖች እየሄነች የመጨረሻው ጦር ቧሂት ላይ ተፈታ፡፡ ዘር የሚቆጥረው መንፈስ በብርቱ ክንድ ተረታና ደረስጌ ዘውዱን ደፋ፡፡
መይሳው ወንዜ አምላኪ ቢሆን መናገሻው ገለጉ በሆነች፤ ግን መጣ፡፡ ጋፋት መሀል ጥበብን ፍለጋ፤ ደግሞም ወረደ መቅደላ ታላቁን የምኞቱን አምባ ሊገነባ፡፡
Henry Stern taken prisoner by Tewodros II in Abyssinia in 1863 Rev Henry Aaron Stern, 1820 to 1885, British missionary Tewodros II, baptized Theodore II c 1818 to 1868 Emperor of Ethiopia From El Mundo en la Mano published 1875

ራስን ማጥፋት ምን ጀግንነት ነው ቢል የዛሬ ሰው አይገርመኝም፤ ዘመን በቆሙበት የሚመተር እውነት አለው፡፡ ስንቱን ዝም ያሰኘው ጀግና ራሱን ሲያጠፋ ፈሪ ተባለ፡፡ በሞት ስርየት እንዳለ ከነበር እንማራለን፡፡
አቤት ያቺ ገጣሚ “የሸዋንም ንጉሥ ሲንቁ ሲንቁ የትግሬንም ንጉሥ ሲንቁ ሲንቁ……” ወንድ አለራስዎ ገለውም አያውቁ አለች፡፡
ታሪክ የጀግንነትን ልክ በሞቱ ለምን ለካው? እንደተወለደ ራሱን ያጠፋ ሰው እኮ አልነበረም፡፡ አይሻል ላይ ድል አጣጥሟል፤ ማን ነክቶኝ ባዩን ራስ አሊን እያሳደደ፡፡
ጉራምባስ የማን ክንድ ታይቶ፤ ግብጥን ከአይማ ወንዝ እስከ ካርቱም ማን አሳደዳት? ደጃች ውቤን ማን ማረከ? በጦር ሜዳ ውሎ ማሸነፍን ለማያውቅ ራስ መግደል ፍርሐት ይሆናል፡፡
ሁሉን አሸንፎ ራስን ስለ ሀገር ክብር አሳልፎ መስጠት ግን የጥቂቶች ናት፡፡ ጥር ነው፡፡ እኒህ ታላቅ ንጉሥ የተወለዱበት ወር፡፡ ገና የምንትዋብ ፍቅር የጀግነነት መንገድ ሲሆን እናያለን፡፡ የጎንደሩን የቁንጅና ውድድር እናነሳለን፡፡ ህልምህን አሳየን ብለን ምኞቱን እመኛለን፡፡ ይቀጥላል…

Sunday, October 15, 2017

በሱማሌ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ በደረሰ የሽብር ጥቃት 85 ሰዎች ሞቱ፡፡

በሱማሌ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ በደረሰ የሽብር ጥቃት 85 ሰዎች ሞቱ፡፡

 ባህር ዳር፡ ጥቅምት 5/2010 ዓ/ም (አብመድ)ሞቃዲሾ ላይ በደረሰው አደጋ ሀላፊነቱን የወሰደ ባይኖርም ሀገሪቱ በተደጋጋሚ የአልቃኢዳ እና አልሸባብ ኢላማ ሆና ቆይታለች፡፡ በተፈጸመው የሽብር ጥቃት ሞቃዲሾ ሀዘን ላይ ነች፡፡ሶማሊያ በፕሬዝዳንት ሙሀመድ ፋርማጆ አማካኝነት 3 የሀዘን ቀናትን አውጃለች፡፡ የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ተነግሯል፡፡ ምንጭ፡-ቢቢሲ

ደብረ ማርቆስ ከተማ ከኦሮምያ እንቦጭን ለማስወገድ ለመጡት ወጣቶች ውብ አቀባበል አድርጋለች፡፡

ደብረ ማርቆስ ከተማ ከኦሮምያ እንቦጭን ለማስወገድ ለመጡት ወጣቶች ውብ አቀባበል አድርጋለች፡፡

 ዛሬ ቀኑ ጥቅምት 2/2010 ዓ/ም ነው፡፡ጥቅምት 2 ደግሞ ኢትዮጵያውን አርበኞች ወራሪውን የጣልያን ፋሺስት በመጣበት እንዲመለስ ‹‹ወረኢሉ ከተህ ላግኝህ›› በተባለው መሠረት የጉዞ መነሻቸው ዕለት ነው፡፡ ዛሬም በጣና ህልውና ላይ የመጣውን ወራሪ ቅጠል ለማስወገድ ከኦሮምያ ክልል ከተለያዩ አካባቢዎች የተሰባሰቡ ወጣቶች ወደ አማራ ክልል በመጓዝ ላይ ናቸው፡፡በአንድነት በመተሳሰብና በመፈቃቀር የተጀመረው ጉዞ ጣና ላይ …ጣናን ባለበት ለማጽናት የሁሉንም ይሁንታ በሚፈልገው ጣና ተገኝተው የድርሻቸውን ይወጣሉ፡፡ወጣቶቹ በአማራ ክልል በሚደርሱበት ቦታ ሁሉ አቀባበል ውብ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡፡፡ የአባይ ገባር የሆነው ጣና ጉዳቱ ከጨመረ መጨረሻው በህዳሴው ግድብ ላይ ሌላ የአደጋ ስጋት ይሆናል፡፡ጣናን መታደግ አባይን መታደግ ነው፡፡ ሁሌም ለስራ ዝግጁ የሆነው የወጣት ጉልበት በእምቦጭ አረም ላይ ዘምቶ ውጤት እንደሚያስመዘግብ ጥርጥር የለውም ፡፡

Saturday, September 9, 2017

የቡርማ ሙስሊሞች ጉዳይ


ከጊዜህ ላይ 90 ሴኮንድ ወስደህ ስለ ቡርማ ሙስሊሞችን ችግር ብታውቅ ምን ይመስልሃል?
ታሪኩ ባጭሩ ይህን ይመስላል!
3,000,000 ሙስሊሞች የሚኖሩባት አራካን የተሰኘች አንዲት ሃገር ነበረች። ከዚች ሃገር ጎረቤት በሆነችው ቡርማ የአራካን ሙስሊሞች በሚያደርጉት ዳዕዋ ምክንያት እስልምና አየተስፋፋ ሄደ። ቡርማ ውስጥ አብዛሃኛው ማህበረሰብ የቡድሃ እምነት ተከታይ ነው። በ1784 /ማለትም ከዛሬ 230 አመታት በፊት/የቡርማ ቡድሂስቶች በአራካን ሙስሊሞች ላይ ባሳደሩት ቂም ምክንያት ወረራ በመፈፀም ብዙ ሙስሊሞችን ገደሉ። አራካንንም ወደ ቡርማ በማስገባት መጠሪያዋን ሚንማር የሚል ስም አደረጉ። ሙስሊሞች አነስተኛውን ቁጥር የሚይዙ ሲሆን ብዛታቸው ከ 3 ― 4 ሚሊዮን ይደርሳል።


በአንፃሩ ደግሞ ቡድሂስቶች 50,000,000 ይሆናሉ።
ሙስሊሞች የራሳቸውን መንደር በማበጀት የንግድ ልውውጦች እና የራሳቸውን ማህበራዊ ህይወት መምራት ጀመሩ። በዚቹ መንደር ውስጥ የተለያዩ ማህበራት ያሉ ሲሆን መሳጂዶችንና ዱኣቶችን ይደጉማሉ።

አሁንም የቡርማ ቡድሂስቶች ወደ ሙስሊሞች መንደር በመዝመት ከሃገር ለማስወጣት እንቅስቃሴ ጀመሩ። ብዙም ሳይቆይ አሰቃቂ የሆነ ግድያ (እርድ) ፈፀሙ። ይህም የሆነው በሙስሊሞች አካባቢ በመዘዋወር ሰዎችን የሚያስተምሩ ፣ ኒካህ የሚያስሩ ፣ ቁርኣን የሚያስቀሩ ወደ አስር የሚጠጉ ሃፊዞችንና ዳኢዎችን በመያዝ ብርቱ የሆነ ድብደባ ፈፀሙባቸው።

ይህም አልበቃ ብሏቸው ሰውነታቸውን በሳንጃ ተጫወቱበት። እንደውም ያንደኛውን ምላስ በገመድ ካሰሩ በኋላ ያለምንም ርህራሄ ጎለጎሉት። ከዚያም ሁሉንም ተራ በተራ እግር እና እጃቸውን በመቆራረጥ ገደሏቸው። ይሄን ሁሉ ግፍ የሚፈፅሙት ለ ኢስላምና ሙስሊሞች ካላቸው ጥብቅ ጥላቻ የተነሳ ነው።

ሙስሊሞችም ከኢማሞቻቸው፣ ከኸጢቦቻቸው እና ከዱኣቶቻቸው ለመከላከል እንቅስቃሴ አደረጉ። ቡድሂስቶችም በአፀፋው የሙስሊሞችን መንደር በእሳት አያያዙት። በእሳት አደጋው የተቃጠሉ ቤቶች ቁጥር ወደ 2600 ገደማ ደርሷል። በዚህም ቃጠሎ ምክንያት የሞተው ሞቶ የሸሸውም ሸሸ። ወደ 90,000 የሚደርሱ ሙስሊሞች በየብስም በባህርም ወደ ሌሎች አገሮች ተሰደዱ።

መታረዱም ይሁን መገደሉ አሁንም ድረስ እንደቀጠለ ነው። ሚስቶቻቸው፣ እህቶቻቸው፣ ልጆቻቸው… አይናቸው እያየ የአስገድዶ መደፈር ወንጀል ተፈፅሞባቸዋል።

Wednesday, September 6, 2017

የ10ኛ ክፍል የፈተና ውጤት ማያ

| የ10ኛ ክፍል የፈተና ውጤት ዛሬ ይለቀቃል

Grade 10 Student Information only.

Use Your Registration No. to check your result.


Click here for Grade 12 result.




ከላይ ካልሰራልወት  ከዚሀ ይጫኑ  እናመሰግናለን!!





© 2017 - NEAEA-Ministry Of Education.
Developers

Monday, September 4, 2017

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ






ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ በራያ የቢራ ማስታወቂያ ላይ በትወና መልክ መሳተፌ የሚታወቅ ነው ሆኖም ለተፈጠረው ስህተት ብዙሁን ቅሬታቸውን በኔ ላይ እያሰሙ ነው:: ነገር ግን እኔ በዚህ ማስታወቂያ ላይ በትወና መልክ ከመቅረብ ውጪ ተፈጠሩ የተባሉ ስህተቶች ላይ አለመሳተፌን ለመግለፅ እወዳለው :: አጥፍቼም ከሆነ ይቅርታ ጠይቃለው ::

Source: ሰላም ተስፋየ facebook account

Wednesday, August 2, 2017

​ቅዱስ ጊዮርጊስ ታደለ መንገሻን ሲያስፈርም አሜ መሐመድን ለማስፈረም ተስማምቷል

የፕሪምየር ሊጉ ቻምፒዮን ቅዱስ ጊዮርጊስ ደደቢትን ለመቀላቀል ተስማምቶ የነበረው ታደለ መንገሻን ባልተጠበቀ ሁኔታ ሲያስፈርም አሜ መሐመድን ለማስፈረም ተስማምቷል፡፡













ያለፉትን ሁለት የውድድር አመታት በአርባምንጭ ያሳለፈው ታደለ መንገሻ ወደ ቀድሞ ክለቡ ደደቢት ለመመለስ ተስማምቶ የነበረ ቢሆንም ባልታወቀ ምክንያት ሳይፈርም ቀርቶ በ2000 እና 2001 የውድድር አመታት ወደተጫወተበት ቅዱስ ጊዮርጊስ ተመልሶ የ2 አመታት ኮንትራት መፈራረሙን የቅዱስ ጊዮርጊስ ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ አስታውቋል፡፡

ሌላው ለቅዱስ ጊዮርጊስ ፊርማውን ያኖራል ተብሎ የሚጠበቀው አሜ መሐመድ ነው፡፡ አሜ ከጅማ አባ ቡና ጋር የ1 አመት ውል የነበረው በመሆኑ ተጫዋቹ ለጅማ አባ ቡና የውል ማፍረሻ 1,000,000 ብር ለመክፈል ተስማምቶ መልቀቂያ ተቀብሏል፡፡ በቀጣዮቹ ጊዜያትም በይፋ ለክለቡ የሚፈርም ይሆናል፡፡

መቐለ ከተማ ሁለት አዳዲስ ተጫዋቾች አስፈረመ

አዲሱ የፕሪምየር ሊግ ክለብ መቐለ ከተማ ጫላ ድሪባ እና ታደለ ባይሳን የግሉ አድርጓል፡፡












ጫላ ድሪባ አዳማ ከተማን ለቆ የተጠናቀቀውን የውድድር አመት በወልድያ ያሳለፈ ሲሆን ከበድሩ ኑርሁሴን ጋር በመፈራረቅ በወልዲያ አጥቂ መስመር ላይ ከአንዷለም ንጉሴ ጋር ሲሰለፍ ቆይቶ ኮንትራቱን በማጠናቀቁ ወደ መቐለ ተጉዟል ፡፡

ሌላው ለክለቡ የፈረመው ታደለ ባይሳ ነው፡፡ ከፋሲል ከተማ ጋር ወደ ፕሪምየር ሊጉ አብሮ ያደገው የመሀል ተከላካዩ ታደለ ዘንድሮ የሊጉ ክስተት በነበረው ፋሲል ከተማ በስፍራው ከከድር ኸይረዲን ጋር በመፈራረቅ የተጫወተ ሲሆን በተሰለፈባቸው ጨዋታዎች ቡድኑን በአምበልነት ሲመራ እንደነበር ይታወሳል፡፡
መቐለ ከተማ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ማደጉን ካረጋገጠ ወዲህ በተጫዋቾች ዝውውር ላይ ተሳትፎን እያደረገ የሚገኝ ሲሆን የሁለቱን ተጫዋቾች ጨምሮ እስካሁን ያስፈረማቸው ተጫዋቾች ቁጥር 5 ደርሷል፡:

ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ 6 ተጫዋቾችን አስፈረመ

ለመጀመርያ ጊዜ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ያደገው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በዛሬው እለት የ5 አዳዲስ ተጫዋቾችን ፊርማ ሲያጠናቅቅ አንድ ተጫዋች በቋሚነት አስፈርሟል፡፡ እንየው ካሳሁንንም ለማስፈረም ተቃርቧል፡፡


ያለፉትን ሁለት አመታት በኢትዮ ኤሌክትሪክ ያሳለፈው ዋለልኝ ገብሬ ወደ ወልዋሎ ማምራቱ የተረጋገጠ ተጫዋች ነው፡፡ የመሀል አማካዩ በኤሌክትሪክ የአማካይ ክፍል ላይ ከበኃይሉ ተሻገር ጋር በመፈራረቅ አመዛኞቹ ጨዋታዎች ላይ መሰለፍ ችሏል፡፡

ቢንያም አየለ ሌላው የክለቡ ፈራሚ ነው፡፡ አዳማ ከተማ በ2007 ወደ ፕሪምየር ሊግ በተመለሰበት አመት 3ኛ ሆኖ እንዲያጠናቅቅ ከተጠባባቂ ወንበር እየተነሳ ባስቆጠራቸው ወሳኝ ጎሎች የረዳ ቢሆንም ቀጥሎ ባሉት አመታት ግን ጥቂት ጨዋታዎች ላይ ብቻ ተሰልፎ ተጫውቷል፡፡

ተስፋዬ ዲባባ ወደ ወልዋሎ ያመራ ሌላው ተጫዋች ነው፡፡ የቀድሞው የሙገር ሲሚንቶ ፣ ኢትዮጵያ ቡና እና ንግድ ባንክ የመሀል ተከላካይ በድሬዳዋ ከተማ ያለፉትን ሁለት አመታት ያሳለፈ ሲሆን በቋሚነትም ቡድኑን አገልግሏል፡፡



ክለቡ ከፕሪምየር ሊጉ በተጨማሪ ሁለት ተጫዋቾችን ከከፍተኛ ሊጉ አስፈርሟል፡፡ ግብ ጠባቂው ዘውዱ መስፍን የባህርዳር ከተማ ውሉን አጠናቆ ወደ ወልዋሎ አምርቷል፡፡ ከዚል ቀደም በቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ መተሀራ ስኳር እና ኢትዮጵያ ክለቦች በፕሪምየር ሊጉ የተጫወተው ዘውዱ ወደ ሊጉ ዳግም ተመልሷል፡፡ እዮብ ወልደማርያምም የወልዋሎ ንብረት የሆነ ተጫዋች ነው፡፡ እዮብ ወልዲያ ወደ ፕሪምየር ሊጉ እንዲገባ ቁልፉን ሚና ከተጫወተ በኋላ ክለቡን ለቆ አመቱን በአማራ ውሀ ስራ አሳልፏል፡፡

ወልዋሎ ካስፈረማቸው አዳዲስ ተጫዋቾች በተጨማሪ አሳሪ አልመሀዲን በቋሚነት አስፈርሟል፡፡ አሳሪ በውድድር አመቱ አጋማሽ ከድሬዳዋ ከተማ በውሰት አምርቶ መልካም ግልጋሎት ማበርከቱን ተከትሎ በቋሚነት ክለቡን ተቀላቅሏል፡፡

እንየው ካሳሁን ለክለቡ ለመፈረም ከስምምነት የደረሰ ተጫዋች ነው፡፡ የቀኝ መስመር ተከላካዩ በአዲስ አበባ ከተማ ያለውን የአንድ አመት ውል ማፍረስ የሚጠበቅበት ሲሆን ውሉን በስምምነት አፍርሶ መልቀቂያውን ሲቀበል ለወልዋሎ በይፋ ይፈርማል ተብሏል፡፡

ወልዋሎ ከቀናት በፊተ የግ መስመር ተከላካዩ ሮቤል ግርማን በሁለት አመት ኮንትራት ማስፈረሙ የሚታወስ ሲሆን የበረከት አማረ ፣ ሳምሶን ተካ እና ኤፍሬም ጌታቸውን ውል ማደሱ ታውቀል፡፡

Monday, July 31, 2017

አባባ ተስፋዬ በ94 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ::

አባባ ተስፋዬ በ94 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ::













ጤና ይስጥልኝ ልጆች!
የዛሬ አበባዎች፤ የነገ ፍሬዎች!
እንደምን አላችሁ ልጆች!
አያችሁ ልጆች!
የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የልጆች ክፍለ ጊዜ ዝግጅት እናንተን ለማስደሰት ልክ በሰዓቱ ይገኛል።
አባባ ደሞ የልጆች ሰዓት እንዳያልፍባቸው በሩጫ ዲ ዲ ዲ ከተፍ ፤ እናንተ ደግሞ ቆማችኃል። ይሄ በጣም ጥሩ ነው ልጆች። አንድ አባት ሲመጣ በአክብሮት መነሳት አስፈላጊ ነው ።
ደህና ሁኑ ልጆች!
ደህና ሁኑ ልጆች!
ነፍሳቸውን በገነት ያኑርልን!

Tuesday, May 23, 2017

ተፈጥሯዊ የእርግዝና መቆጣጠሪያ

ተፈጥሯዊ የእርግዝና መቆጣጠሪያ

የወር አበባ ኡደትን ማዕከል ያደረገ
ውድ የሳይቴክ ፔጅ ተከታታዮች፡፡ የወር አበባ ኡደትን ማዕከል ያደረገ የወሊድ መቆጣጠሪያ ይሄንን ይመስላል፡፡
• የወር አበባ መፍሰስ ከጀመረበት ቀን አንስቶ እስከ አምስተኛው ቀን ድረስ መደበኛ የወር አበባ ጊዜ ነው፡፡ ይሄንን ጊዜ ጨምሮ የወር አበባው ከጀመረበት ቀን እስከ 8ኛው ቀን ድረስ (የመጀመሪያዎቹ ሰባት ቀናት) በአንፃራዊነት እርግዝና አይፈጠርም፡፡ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት በዚህ ወቅት ያለመፈጠር እድሉ ከ95-100% እንደሆነ ይደርሳል፡፡
• ከ8ኛው ቀን እስከ 11ኛው ቀን ባሉት ሶስት ተከታታይ ቀናት ደግሞ በአንፃራዊነት እርግዝና ሊፈጠር ይችላል፡፡ ጥናቶቹ የሚጠቁሙትም እርግዝና የመፈጠሩ እድል ከ40-60% ይደርሳል፡፡
• ከ11ኛው ቀን ጀምሮ እስከ 17ኛው ቀን ድረስ ባሉት ተከታታይ 6 ቀናት እርግዝና የመፈጠር እድሉ እጅግ በጣም ከፍተኛ ነው፤ ከ80% በላይ፡፡
• ከ17ኛው ቀን አንስቶ እስከ 20ኛው ቀን ድረስ ባሉት 3 ተከታታይ ቀናት ደግሞ በአንፃራዊነት እርግዝና ሊፈጠር ይችላል፡፡ ጥናቶቹ የሚጠቁሙትም እርግዝና የመፈጠሩ እድሉ ከ40-60% እንደሆነ ነው፡፡
• ከ20ኛው ቀን አንስቶ የወር አበባ እስከሚመጣበት ጊዜ ድረስ እርግዝና አይፈጠርም፡፡ በዚህ ወቅት እርግዝና ያለመፈተሩ እድል ከ95-100% ይደርሳል፡፡
• የሴቷ እንቁላል በወር አበባው ኡደት እኩሌታ ቀን ላይ (28 ከሆነ 14ኛው ቀን ላይ) ዝግጁ የሚሆን ሲሆን ከ12-24 ሰዓታት ለሚሆን ጊዜ ለፅንስ ዝግጁ እንደሆነ ሊጠብቅ ይችላል፡፡ በአንፃሩ የወንዱ የዘር ፍሬ ከወሲብ በኋላ በሴቷ ማህፀን ውስጥ ከ3 እስከ 5 ቀናት ሊቆይ የሚችል ሲሆን በአንድ ላይ ሲደመር ከአምስት ቀን እስከ ሰባት ቀናት ለሚሆን ጊዜ የእርግዝናው እድልን እጅግ ከፍተኛ ይሆናል ማለት ነው፡፡
ሌሎችም ያንብቡት። በተን በተን አርጉት።

Saturday, May 20, 2017

ለራስ ምታት ፍቱን የሆኑ 9 የምግብ አይነቶች

ለራስ ምታት ፍቱን የሆኑ 9 የምግብ አይነቶች


















1. ሃብሃብ

ሃብሃብ - በውስጡ እጅግ ብዙ ፈሳሽ እና ማዕድናትን የያዘ ከፍራፍሬዎችም በትልቅነቱ የሚታወቅ ነው፡፡ በተለይ ከአዲስ አበባ ወደ ናዝሬትና ሐዋሳ መስመር ሲሄዱ በመንገድ ዳር ተሸክመው ሲሸጡት እንመለከታለን፡፡ ሞክረውት እንደሆነ ባላውቅም በጉዞው ወቅት ለሚኖረው ሙቀት እና የውሃ ጥም ሁነኛ መፍትሄ ሆኖ ይገኛል፡፡ ከዚህ ጥቅሙም ባሻገር ለራስ ምታት ፍቱን መድሃኒት መሆኑ በባለሙያዎች ተጠንቶ ተቀምጧል፡፡ የሪደርስ ዳይጀስት መጽሔት በቅርቡ ባሰፈረው ጽሑፍ ሃብሃብ ለራስምታት ፍቱን ያስባለው ከፍተኛ የውሃ እና ማዕድናት በተለይም ከፍተኛ የማግኒዚየም ማዕድን መጠኑ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ለራስምታት ከሚያጋልጡ ምክንያቶች አንዱ ድርቀት ወይም በሰውነት ውስጥ በቂ ፈሳሽ ያለመኖሩ ነው፡፡ ይህ ፍራፍሬ ደግሞ ይህን ችግር በደንብ ይፈታል፡፡ ከራስ ምታት ክኒን ይልቅ በቅርብ ሃብሃብ ከተገኘ በደቂቃዎች ውስጥ ከራስምታቱ እረፍትን ይሰጣል ብለው ባለሞያዎቹ ይናገራሉ፡፡

2. ዝንጅብል

ዝንጅብል ላይ የሚደረጉ ምርምሮች ገና በቅርቡ የተጀመሩ ቢሆንም በውስጡ የደም ቧንቧዎችን መቆጣት እና ህመም የሚቀንሱ መድሃኒቶች ውስጥ ካሉ ኬሚካሎች ጋር ተመሳሳይ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን ተመራማሪዎች ማግኘት ችለዋል፡፡ በተለይ በከባድ የራስ ምታት ወቅት የደም ቧንቧዎችን መቆጣት በማስከተል ራስምታቱ እንዲቀሰቀስ የማድረግ ተግባር ያላቸውን ፕሮስታግላንዲን የሚሰኙ ንጥረ ቅመሞች መጠን በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነስ ራስ መታቱን እንደሚያስታግስ የሪደርስ ዳይጀስት መጽሔት ይገልጣል፡፡ ራስ ምታቱን ሙሉ በሙሉ ባያቆመው እንኳ ከራስ ምታት ጋር የሚመጡ ደስ የማይሉ እንደ ማቅለሽለሽ አይነት ስሜቶችን በቶሎ ይቀንሳል፡፡ ለዚህ ሳይሆን አይቀርም ኢትዮጵያውያን ያለጥናቶቹ ውጤትም ቀድመው ለሆድ ህመም እና ማቅለሽለሽ ዝንጅብል አኝክበት ሲሉ የኖሩት!

3. ቡና

ለአንዳንዶች ቡና ፍቱን የራስ ምታት መድሃኒት ሲሆን ማይግሬይን ላለባቸው አንዳንድ ሰዎች ላይ በብዛት ሲወሰድ ማይግሬይኑን የሚቀሰቅስበት አጋጣሚ አለ፡፡ ሳይንሱ ሁሉንም የቡና ምስጢር ፈትቶ ባይጨርስም እስካሁን ባሉት ጥናቶች መሰረት ግን ቡናን ፍቱን የራስ ምታት መድሃኒት አድርጎ መውሰድ ይቻላል፡፡ መጠኑን በልክ ማድረግ አብሮ ሊታሰብበት ይገባል፡፡ ለከባዱ የራስ ምታት ማይግሬይን የሚታዘዙ ክኒኖች ውስጥ የቡና ዋና ንጥረ ነገር ካፌይን ይገኛል፡፡ ስለሆነም ቡና ለራስ ምታት በመፍትሄነት መቅረቡ አስደናቂ ነገር አይሆንም፡፡ ይሁንና መጠኑ በበዛ ቁጥር ራስ ምታትን ከማስታገስ ይልቅ ጭራሽ ሊቀሰቅሰው ይችላል፡፡ እጅግም ወፍራም ያልሆነ አንድ ወይም ሁለት ስኒ ቡና ከሁለት ክኒን የተሻለ ተፈጥሯዊ መድሃኒት ሆኖ ተገኝቷል፡፡

4. ስፒናች

ትኩስ ስፒናች ጎመን ቅጠል በውስጡ የያዛቸው ቅመሞች ራስ ምታትን በማስታገስ ብቻ ሳይሆን የደም ግፊት መጠንን በመቀነስም በቀደመው ጊዜ ጥቅም እንደነበራቸው መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ አትክልትና ፍራፍሬ በርካሽ ለሚገኝባቸው እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ሀገራት ይህ ጥሩ ዜና ይመስላል፡፡ በውጪው ዓለም ስፒናችን አብስሎ ወይም በትኩሱ ከቲማቲም ጋር ከትፎ በመብላት ብቻ ሳይሆን ጨምቆ ከመጠጣትም ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ የቅርብ ጊዜ ጥናቶች ደግሞ ይህ ፍቱን አትክልት ለራስ ምታትም ፈጣን መፍትሄ ይሰጣል ብለዋል፡፡ ቢፈልጉ ጨምቀው ከሻይ ጋር አለዚም ባዶውን ወይም ትኩሱን ቅጠል ሰላጣ እንደሚያዘጋጁት አዘጋጅተው ቢመገቡት ከራስ መታቱ ፋታ እንዲያገኙ እንደሚረዳዎት የተደረጉ የመጀመሪያ ደረጃ ጥናቶች አመልክተዋል፡፡

በተጨማሪም
5. ሙዝ፣

6. እርጎ፣

7. ጉበት፣

8. ድንች እና

9. ቃሪያም ራስ ምታትን በመቀነስ በኩል ፍቱን እንደሆኑ በጥናት ተረጋግጥዋል፡፡

ሌሎችም ያንብቡት። በተን በተን አርጉት።
ጤና ለሁሉም!

Tuesday, May 16, 2017

የቪዛ መስፈርቶች ለኢትዮጵያ ዜጎች

የቪዛ መስፈርቶች ለኢትዮጵያ ዜጎች በየአገሩ ይለያያሉ። የኢትዮጵያ ዜጎች ወደ ብዙዎቹ አገራት ለመግባት፣ አስቀድሞ ከዚያው አገር ኤምባሲ ወይም ቆንስላ በፓስፖርት ውስጥ የቪዛ (መግቢያ ፈቃድ) ማሕተም ማግኘት አስፈላጊነት ነው። ሆኖም አንዳንድ አገር ያለ ምንም ቪዛ ሂደት ኢትዮጵያውያን ለተወሰነ ጊዜ እንዲጎብኙ ይፈቅዳል፣ እንዲሁም አንዳንድ አገር ኢትዮጵያውያን እዚያ በደረሱበት ጊዜ የመግቢያ ፈቃድ ይሰጣል።



ማስታወሻ - መስፈርቶቹ እንደ መንግሥታት በቶሎ ሊቀየሩ ይቻላል።


ያለ ቪሳ መግባት የፈቀዱ አገራት

  • ኬንያ - ለ3 ወር ያለ ቪሳ መጎብኘት ለኢትዮጵያውያን ይፈቀዳል
  • ሃይቲ - ለ3 ወር " " " "
  • ሴኔጋል - ለ3 ወር " " " "
  • ቤኒን - ለ90 ቀን " " " "
  • ሴይንት ቪንሰንትና ግሬናዲንስ - ለ30 ቀን " " " "
  • ሲንጋፖር - ለ30 ቀን " " " "
  • ማይክሮኔዥያ - ለ30 ቀን " " " "
  • ፊሊፒንስ - ለ30 ቀን " " " "
  • ዶመኒካ - ለ21 ቀን " " " "

ኢትዮጵያውያን በደረሱበት ጊዜ የጉብኝት ቪሳ የሚሰጡ አገራት

እነዚህን አገራት ከመግባት በፊት ቪሳ ማግኘት አስፈላጊ አይደለም። ሌሎች አገራት ሁሉ ግን ከመግባት አስቀድሞ ቪሳ ማግኘት አስፈላጊነት ነው።
  • ኮሞሮስ
  • ካቦ ቨርዴ
  • ጂቡቲ
  • ኡጋንዳ
  • ሞሪታኒያ
  • ርዋንዳ
  • ደቡብ ሱዳን
  • ማዳጋስካር (የ90 ቀን ጉብኝት ቪሳ)
  • ቦሊቪያ (የ90 ቀን " ")
  • ጊኔ-ቢሳው (የ90 ቀን " ")
  • ኒካራጓ (የ90 ቀን " ")
  • ሞሪሸስ (የ60 ቀን " ")
  • ታጂኪስታን (የ45 ቀን " ")
  • ሰይንት ሉሻ 6 ሳምንት " "
  • ሞዛምቢክ (የ30 ቀን " ")
  • ጋና (የ30 ቀን " ")
  • ካምቦዲያ
  • ላዎስ (የ30 ቀን " ")
  • ምሥራቅ ቲሞር (የ30 ቀን " ")
  • ታይላንድ (የ15 ቀን " ")
  • ኢራን (የ15 ቀን " ")
  • ቶጎ (የ7 ቀን " ")
  • ሳሞአ - ለ60 ቀን " " " "
  • ሲሸልስ - ለ3 ወር " " " "
  • ቱቫሉ - ለ1 ወር " " " "
  • ማልዲቭስ - ለ30 ቀን " " " "
  • ፓላው - ለ30 ቀን " " " "

በኢንተርኔት ላይ ቪዛ የሚስጡ አገራት

  • ጂዮርጂያ
  • አንቲጋ እና ባርቡዳ
  • አውስትራሊያ
  • ጋቦን
  • ስሪ ላንካ

የኢትዮጵያ ዜጎች የማይፈቅዱ አገራት

  • ኩዌት

Monday, May 15, 2017

የጌሾ መድሃኒታዊ ጥቅም እና ሌሎች ጥቅሞች



ጌሾ በአፍሪካ ብቻ የሚበቅል በተለይ በኢትዮጵያና በደቡብ አፍሪካ የሚገኝ ተክል ነው። በኢትዮጵያ ጠላና ለጠጅ ሲጠመቅ ጌሻ ይገባል። የሚበቅለውም ከባህር ወለል በላይ 1400-3200 ሜትር ላይ ነው።

መድሃኒታዊ ጥቅም

-ቆረቆርና ሌሎች የፈንገስ በሽታወችን በደቀቀ ፍሬውና ቅጠሉ በመቀባት ለማዳን ይቻላል - ህጻናት እንጥላቸው ከተቆረጠ በኋላ ህመማቸውን ለማስታገስ አፋቸው ውስጥ የጌሾ ቅጠል ይደረጋል -ቂጥኝ በሽታን ለመከላከል -ሆድ ድርቀት ለማስወገድ - ሥሩ ደምን ለማጥራት ያገለግላል

ሌሎች ጥቅሞች

የጌሾ ግንድ በጣም ጠንካራ ስለሆነ ለተለያዩ የእንጨት ውጤቶች ሊያገለግል ይችላል። የጌሾ ዛፍ በምንጮች አካባቢ ቢተከል የመሬት መሸርሸርን ሊከላከል ይችላል። ከእርሻ ማሳ ዳርቻ ላይ በመትከልም የመሬትን ንጥር ነገር ከነፋስ እና ከዝናብ መከላከል ይቻላል። የጌሾ አበቦች በንቦች ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነት ስላላቸው የጌሾ ተክል ለንብ እርባታና ለማር ምርት ከፍተኛ ግልጋሎት ሊሰጥ ይችላል።

የሩዝ ቅቅል አዘገጃጀት ለ3 ሰው


አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች 3 የቡና ስኒ (300 ግራም) ሩዝ 1 መካከለኛ ጭልፋ (150 ግራም) የደቀቀ ቀይ ሽንኩርት 6 የሾርባ ማንኪያ ዘይት 1 የሻይ ማንኪያ ጨው 1 የሻይ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ፡፡




 አዘገጃጀት 
1. ሩዙን በደንብ አጥቦ ደረቅ እስኪል ማንጠፍጠፍ፤ 
2. ዘይት በደረቅ ብረት ድስት ውስጥ አሙቆ ቀይ ሸንኩርቱን በመጨመር ማቁላላት፤ 
3. ሩዙን በላዩ ጨምሮ ደርቆ ቀላ ያለ መልክ እስኪያወጣ ማቁላላት፤ 
4. ሩዙ በተለካበት ዕቃ እጥፍ የሚሆን ውሃ መጨመር፤ 
5. አንዴ ብቻ አማስሎ እስኪበስል መተው፤ 
6. ጨውና ቁንዶ በርበሬውን ጨምሮ ማስተካከል፤ 
7. ውሃው መጦ ሲበስል ማውጣት፤ 
8. ውሃው መጦ ሩዙ ካልበሰለ በማንኪያ መሃሉ ላይ ወጋ አድርጎ የፈላ ውሃ በመጨመር እንደገና እስኪመጥ መጠበቅና ለገበታ ሲፈለግ ከሶሱ ጋር ደባልቆ ወይም ለየብቻ ማቅረብ፡፡